በባህሬን የፋሲካና የረመዳን ፆም ፍቺ በዓል የማክበርና አዳዲሰ የኮሚዩኒቲ አባላትን የማስመርጥ ፕሮጋራም ተካሄደ።

የፋሲካና ረመዳን ፆም ፍቺ በዓል ምክንያት በማድረግ በሚሲዮኑ አዘጋጅነት ግንቦት 02 ቀን 2016 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ውሏል።

በዝግጅቱ ላይ በባህሬን የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያዊያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን፣ የኢትዮጵያውያን ወዳጆችና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች የተገኙ ሲሆን የዝግጅት መርሃ ግብሩ በኢትዮጵያ ብሄራዊ መዝሙር እና በባህሬን የኢትዮጲያዊያን የሃይማኖት አባቶች ጸሎተ ቡራኬ ተከፍቷል።

ከዚሁ በመቀጠል በባህሬን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስል ጄኔራል ክቡር አምባሳደር ሽፈራው ገነቲ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸውም ወቅት ለረመዳንና ፋሲካ ጾም ፍቺ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤቱ በመስራት ላይ ከሚገኛቸው ሥራዎች መካከል የዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲን ማጎልበት እንዱ መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህን ስራ ደግሞ በሚገባ መስመር ይዞ እንዲሄድ፣ በሀገሩ የሚኖሩ ዜጎቻችንን በተለያዩ ማህበራት ማደራጀትና በማጠናከር ሀገራዊ ፍቅር የለው ማህበረሰብ ለመገንባት የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።

ክቡር አምባሳደር በመቀጠልም መንግስት ሀገራዊ የእርቅ ኮሚሽንን አቋቁሞ ወደ ሥራ በማስገባት በአገር ቤት የሚታዩ ችግሮችን በእርቅና ውይይት እንዲፈቱ የማድረግ ሥራ እየሰራና፣ ከፍተኛ የልማት ስራዎችን በማከናወን፣ ለዜጎች ሰፊ የስራ እድል በመፍጠር ላይ መሆኑን በማስታወስ፣ በአሁን ጊዜ ፅዱ ኢትዮጵያን ለመገንባት “ፅዱ ጎዳና ኑሮ በጤና“ በሚል አገር አቀፍ የገቢ ማስባሰቢያ ንቅናቄ እየተደረገ መሆኑን ገልጸው በባህሬን የሚኖሩ የዲያስፖራ ማህበረሰብም በዚህ ሀገራዊ ልማት ላይ የእራሳቸውን አሻራ እንዲያኖሩ ጥሪ አቀርቧል።

በተጨማሪም ከዚህ በፊት በማህበረሰቡ ተመርጠው ባለፉት ጊዜያት ሲያገለግሉ ለቆዩ የኮሚዩኒቲ አደረጃጀት አባላት ሽኝት በማድረግ፣ ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል ባማከለ መልኩ አዳዲሰ የኮሚዩኒቲ አባላትን በማስመረጥ፣ በታዳሚዎች አስተያየት እንዲሰጥባቸው የማድረግ ፕሮግራም ተከናወኗል።

በመጨረሻም የኃይማኖት አባቶችና የውይይቱ ተሳታፊዎች በአገር ቤት በመካሄድ ላይ ስላሉ ፕሮጀክቶች ሰለተደረገላቸው ገለጻ፣ የኮሚዩኒቲ አደረጃጀትን ለማጠናከር በተሰሩ ስራዎች እንዲሁም የረመዳንና የፍሲካ በዓልን አስመልከቶ ለተደረገላቸው ዝግጅት ምስጋናቸውን አቅርቧል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook