በባህሬን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስል ጄኔራል ክቡር አምባሳደር ሽፈራው ገነቲ፣ ከAlmeer Group B.S.C  CEO Mr. Abdulla Almeer, VP of Construction and Trading  Sector Mr. Jalal Almeer እና Almeer Distribution General Manager Mr. Aasem Almeer ጋር ነሀሴ 27 ቀን 2016 ዓ/ም በሚሲዮኑ ተገኝተው በንግድና ኢንቨስትመንት ዙሪያ ተወያዩ።

በውይይታቸው ክቡር አምባሳደር በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን የገለጹ ሲሆን በንግዱ ዘርፍ ካምፓኒው የግብርና ምርቶች፣ አትክልትና ፍራፍሬ ከአገራችን ማስመጣት በሚችሉበት መንገድ፣ ኢትዮጵያ ከአለም ከፍተኛ የቁም እንስሳት የሚገኝባት አገር መሆኗን ጠቅሰው ካምፓኒው ያለውን የገበያ አማራጭ እንዲጠቀም ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፣ ቆንስላ ጽ/ቤቱ አስፈላጊውን ትብ   ብር እንደሚያደርግ ለዋና ስራ አስፈጻሚው ገልጸውላቸዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው በበኩላቸው ካምፓኒው የኮንስትራክሽን እቃዎችን፣ የሱፐርማርኬት እቃዎችን በማስመጣት በባህሬን ለሚገኙ ትላልቅ ሱፐርማርኬቶች እንደሚያከፋፍልና በኢትዮጵያ ያለውን ገበያ እድል መጠቀም እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።

በመጨረሻም ክቡር አምባሳደር የካምፓኒው ሀላፊዎች በኢትዮጵያ ጉብኝት እንዲያደርጉ የጋበዙ ሲሆን ቆንስላ ጽ/ቤቱ ማንኛውም አይነት ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው ገልጸውላቸዋል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook