የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት በባህሬን የኢትዮጵያዊያን ኮሚዩኒቲ ማህበር አዲስ ከተመረጡ አመራሮች ጋር ትውውቅ በማድረግ በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አደረገ፤

ግንቦት 26 ቀን 2016 ዓ.ም. የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት በባህሬን የኢትዮጵያዊያን ኮሚዩኒቲ ማህበር አዲስ ከተመረጡ አመራሮች ጋር በመተዋወቅ በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል።

በማህበረሰቡ ተመርጠው ባለፉት ጊዜያት ሲያገለግሉ ለቆዩ የኮሚዩኒቲ አደረጃጀት አባላት ሽኝት በማድረግ፣ ለቀጣይ ሁለት አመታት እንዲያገለግሉ የተመረጡ የኮሚዩኒቲ አመራሮች በሚሲዮኑ በመገኘት ከክቡር አምባሳደር ሽፈራው ገነቲ ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን ከዚህ በፊት በነበሩ የኮሚዩኒቲ አመራሮች ላይ ሲስተዋሉ የነበሩ ክፍተቶች እንዳይደገሙ በማድረግ በቀጣይ ኮሚዩኒቲውንና አገራቸውን በቅንነት ለማገልገል ቃል ገብቷል።

ክቡር አምባሳደር ሽፈራው ገነቲ በበኩላቸው የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ በመጠቀም የዜጎቻችን መብትና ጥቅም ከማስጠበቅ ጎን ለጎን በኮሚዩኒቲ መተዳደሪያ ድንብ መሠረት የአገራችን ገጽታ በሚያጎለብቱ ኩነቶች ላይ ትኩረት በማድረግ መስራት እንዳለባቸው አፅንኦት ስጥተው መክረዋል።

ከቡር አምባሳደር በመቀጠል በአገር ቤት እየተከናወኑ ስላሉ ዘርፍ ብዙ የልማት እንቅስቀሴዎች ገለጻ በማድረግ በክቡር ጠ/ሚኒስትራችን ይፋ ሆኖ እየተተገበረ ያለው “ጽዱ ጎዳና – ኑሮ በጤና” ፕሮጄክትና ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ማህበሩ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አስተላልፈዋል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook