ከዜጋ ተኮር ስራዎች ጋር በተያያዘ ብዙ ስራዎች እንደሚሰሩ ይታወቃል። ይሁን እንጂ ዜጎቻችን ለዓመታት ሰርተው የጉልበታቸው ዋጋ ሳይከፈላቸው ወደ ቆንስላ ጽ/ቤታችን ማመልከት እንዳይችሉ በማድረግ የመብት ጥሰት የሚደርስባቸው ሲሆን ከዚህም ውስጥ ከዓመታት በላይ ያለምንም ክፍያ የሰሩትን ዜጎች ጉዳያቸውን ወደ ሚመለከታቸው መንግስታዊ አካላት በማቅረብ ያልተከፈላቸው ደመወዝ በውላቸው መሠረት እንዲያገኙ እየተደረገ ይገኛል። ከነዚህም መካከል ጋዲሴ አቡሌ የተባለች ዜጋችን የሰራችበትን የ1 ዓመት ከ4 ወራት በላይ ደመወዟን አሰሪዋ ሳይከፍላት ስለመቅረቱ መረጃው ስለደረሰን ጉዳዩን ወደ ፖሊስ ጣቢያ በመውሰድ ክትትል ስናደርግ ቆይተን ያልተከፈላት ደመወዟ እንዲከፈላት አስደርገናል።

በዚህም መሠረት ዜጎቻችን የተለያዩ የመብት ጥሰቶችና ችግሮች የሚደርስባችሁ ከሆነ ከአሰሪዎቻችሁ ቤት መጥፋት ሳያስፈልግ በቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤታችን ውስጥ ወደሚሰሩ ሰራተኞች በመደወልና መረጃ በመስጠት ጉዳያችሁ መፍትሄ እንዲያገኝ የሚደረግ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።

 

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook